በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑካን ቡድን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 09 ስር በሚገኘው ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 18/2017 ዓ.ም
በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልኡካን ቡድን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገኘት በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሪፎርም ስራዎች ላይ ምልከታ በማድረግ የልምድ ልወውጥ ተካሒዷል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ኒዕመተላህ ከበደ ለልዑካኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶች፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ የተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎች፣ ምቹ የስራ አከባቢ ከመፍጠር ጀምሮ አጠቃላይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን በተለይ አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ለማዘመን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተሰራበት መንገድ እንዲሁም በትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማሻሻል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ልምዳቸውን አካፍለዋል ።